loader image

ግብረመልሰ እናበረታታለን

ግብረመልሰ እናበረታታለን

ግብረመልሰ እናበረታታለን!

የተወደዳችሁ ወጣት መሪዎች! ይህ ምላሻችሁን ለመሻት የቀረበ ጥሪ ነው!

በቅርቡ “ለኢትዮጵያ ወጣት መሪዎች በፌዴራል የመንግስት አስተዳደር , በዲሞክራሲ ሥርዓት እና ሰላም ግንባታ ቀዳሚ እርምጃ” ላይ የሚያጠነጥን የምክክር ሥልጣና መካሄዱን እናሰታውሳለን፡፡ በሲዲሲቢ እና ፌዴሬሽኖች ፎረም የተዘጋጀው ይኸው ሥልጠና በ5 ተከታታይ ዙሮች ለእያንዳንዱ ለ4 ቀናት ቆይታ የተከናውነ ነበር፡፡ በሥልጠናው ሂደት በተሳታፊ ወጣቶች መካከል የነበረው ምክክር ሞቅ ያለ እና በጣም የሚያበረታታ እንደነበር በሚገባ እናምናለን፡፡ ይህ በመሆኑም ነው በሀገሪቱ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በየደረጃው ማስፋፋቱ አስፈላጊ መሆኑን ከናንተው ጋር የተማምንበት፡፡ በወቅቱ ከሀገሪቱ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ከተለያዩ ዘርፎች ለሥልጠናው የተሰባሰቡት ወጣት መሪዎች የጨበጧቸውን ፍሬነገሮች ለሌሎች ያካፍላሉ ብለን እናምናለን፡፡

በሥልጠናው ወቅት ከነበረው ልባዊ መነሳሳት አኳያ ወጣት መሪዎቹ በየሥራ ቦታዎቻቸው እና በየመኖሪያ አካባቢዎቻቸው የሥልጠና ውይይቱ ያተኮረባቸውን ጉዳዮች ጭብጦች ለሌሎች አስር አስር ሰዎች እንደሚያካፍሉ እርግጠኞች ነበርን፡፡ በየሥልጠናው ማጠቃለያ ላይም የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሆነው ሲዲሰቢ (CDCB) እና የፌዴሬሽኖች መድረክ  (Forum of Federations) ይህንኑ መልእክት ለወጣት መሪዎቹ አስተላልፈዋል፡፡ ተሳታፊ ወጣቶቹም ሀሳቡን በማድነቅ በዚሁ መሰረት እነንደሚተገብሩ ቃል ገብተው ነበር፡፡

ምንም እንኳ እስከዛሬ ድረስ በቂ ግብረመልስ ያላገኘን ቢሆንም አሁን አልዘገየም ብለን እናምናለን; ሆኖም ፈጣን ምላሻችሁን ለማግኘት የማሳሰቢያ ወቅት መሆኑንም ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ የሥልጠናው ተሳታፊ የነበሩት ሁሉም ወጣት መሪዎች በአይቲ ኤክስፐርቶቻችን በተሰጣችሁ የመስመር ላይ አድራሻችን ግብረመልስ እንደምትሰጡን እንጠብቃለን፡፡ የሥልጠና ምክክሩን ለሌሎች የማዳረስ ሥረዎችን በፎቶግራፍ በቪዲዮ ወይም በአርት መልክ በማዘጋጀት እንድትልኩልን እንፈልጋለን፡፡  

የተዋጣለት ሥራ ሠርቶ ለኛ በመላክ ረገድ በእርግጥ እስካሁን ባለው ጊዜ ምላሽ ባለማግኘታችን የግድ ምላሽ መስጠት ነበረባችሁ ብለን አላማረርንም፡፡ በሌላ በኩልም አላሰፈላጊ መጓተት እንዲኖርም አናበረታታም፡፡ ምክንያቱም ጊዜ ባለፈ ቁጥር ለሌሎች ማስተለለፍ የሚገቡን የሥልጠናው ፍሬ ሃሳቦች እየተረሱ የመምጣታቸው እድል ሰፊ ይሆናልና ነው፡፡  

በመሆኑም በሀገራችን እንዲሰፍን የሚፈለገው የመልካም አስተዳደር ዲሞክራሲ እና ሰላም ግንባታ ለውጥ እንዲመጣ በጋራ የመስራት መንፈስን ለማጠናከር እንሻለን፡፡ እባካችሁ ፕሮራሙን አስፋፍተን ለመቀጠል ጭምር እንዲያግዘን ጥያቄዎች ካሏችሁ አክላችሁ ግብረመልሳችሁን በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ላኩልን፡፡ ለአማራጭ እንዲሆናችሁም cdcb2020@gmail.com የሚለውን መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አማኑኤል አድነው

አግዜክዩቲቭ ዲሬክተር 

Previous We encourage feedback

Connect With Us

Meskel Square Science and Technology Building 5th Floor

Mon – Fri: 8:00 am – 5:00 pm

P.O. Box: 25024 Code 1000

Join the Community

Get latest CDG news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Copyright © 2022 CDCB | Powered by CDCB