የወጣት መሪዎች ምክክር በአገር ጉዳይ ላይ

ወጣት መሪዎች በመልካም አስተዳደር እና በሰላም ላይ ያላቸውን ሚና ለማጉላት የሚያስችል የ4 ቀናት ምክክር መድረክ ከትናት ጀምሮ በቢሾፍቱ/ደብረዘይት ድሪምላንድ ሪዞርት ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ለሁለተኛ ዙር በመካሄድ ላይ የሚገኘው የምክክር መድረክ የሚወያይባቸው ጉዳዮች የፌደራል አስተዳደርን ዲሞክራሲን ሰብአዊ መብቶችን እና ሰላምን የሚያካትት ነው፡፡ የምክክር መድረኩ የተዘጋጀው ዋና ጽ/ቤቱ ካናዳ በሚገኘው የፌዴሬሽች ፎረም እና በሴንተር ፎር ዲቨሎፕሜንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢልዲንግ አገር በቀል መያድ የጋራ ቀንጅት ነው፡፡

 

በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተከበሩ አቶ ታየ ደንዳአ የሰላም ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዴታ ነበሩ፡፡ ሚኒስትር ዴታው የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች በአራት ቀናቱ ውይይታቸው ወቅት የውይይቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑና አገሪቱን በአሁኑ ወቅት የገጠሟትን ፈታኝ ሁኔታዎች በጋ ለመፍታት በሚያስችሉ እሴቶች ታጥቀው ወደየመስካቸው እንዲመለሱ አበረታተዋል፡፡

አቶ ደሳ ቡልቻ የፌዴሬሽኖቹ ከፍተኛ ዳይሬክተር በፌዴሬሽኖቹ ላይ እና ሲዲሲቢ ሥራውን ለማከናወን ፍላጎት እና ዝግጁነቱን በማሳየቱ ከነሱ ጋር ይህ  ሥልጠና መዘጋጀቱን አስመልክተው አንዳንድ የዳራ ነጥቦችን አመልክተዋል፡፡

አቶ አማኑኤል አድነው የሲዲሲቢ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ተሳታዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለው ስለሲዲሲቢ እና ስለሥልጠናው አንዳንድ አጠቃላይ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ በዚሁ ንግግራቸው ሴንተሩ የሀገሪቱን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ አግባብነት ያላቸው ጥናቶች እንዲካሄዱ የቡሉን ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሲዲሲቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ምሁራንን እና ታዋቂ ሰዎችን ያሳተፉ ልዩ ልዩ መድረኮችን ሲያዘጋጅ መቆቱን አብራርተዋል፡፡ አሁን እየተካሄደ ያለውን ሥልጠና አስመልክተውም ጥናቱ የተዘጋጀው ለዚሁ ሲባል የተናቀረውን የጥናት ማኑዋል መሰረት አድርጎ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሥልጠናው በቀጣይ 3 ሳምንታትም በተከታታይ ከማክሰኞ እስከ አርብ በሚኖሩት ቀናት በሌሎች 3 የሠልጣኞች ቡድን እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡